በኩዌት ውስጥ የኮሮና ወረርሽኝ ከተከስተ ጀምሮ በቤት ስራተኞች አያያዝ እና የስራ ጫና ላይ ከአለም አቀፉ የስራተኞች ማህበር አላፉዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል ።
በማህበራችን አማካኝነት በቀረበው ጥናት እና ዜጎቻችን በየጊዜው ያሉበትን ሁኔታ ፣ የደሞዝ ክፍያ ፣ የስራ ጫናና ፣ በቂ ዕረፍት አለመኖር እንዲሁም ደሞዝ ክልከላን ጨምሮ ባሉ መስል ችግሮች ዙሪያ ውይይት እና የመፍትሄ ሃሳቦች ቀርበዋል ።
የህንድ ፣ፍሊፕኒስ፣ብሩኪና ፋሶ ፣አይቬሪኮስት፣ ዜጎችን ተመርኩዞ በቀረበው ውይይት ዙሪያ በስራተኞቹ በኩል የቀረቡ ችግሮች እና ሀሳቦች ለሚመለከተው የመንግስት አካል እንደሚቀርብ ተገልጿል ።
በተጨማሪም ማህበሩ ባመቻቸው ስልጠና ላይ ተሳታፊ ለሆኑ ዜጎች የሚስጠው ስልጠና የቀጠለ ሲሆን በተቻለ መጠን በኢትዬጵያውያን የቤት ስራተኞች ማህበር ስር ላሉ ስልጣኞች ቀጣይነት ባላቸው የልምምድ ስራዎች ላይ የተጀመሩ ስራዎችም እንደሚቀጥሉ ታውቋል ።