Event Details

የኢትዬጵያ ኮሚዩኒቲ የኢፍጣር የእራት ግብዥ አደረገ ።

05 May 2019

 

በኩዌት የኢትዬጵያ ኮሚዩኒቲ ( ማህበረስብ ) ማህበር በኩዌት ለሚገኙ ኢትዬጵያውያኖች በ29/05/2019 በኢትዬጵያ ኤምባሲ የመስብስቢያ አዳራሽ የኢፍጣር ፕሮግራም አካሂዷል ።
ክቡር አምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ እና የኤምባሲው ዲፕሎማቶች ፣ የቀድሞ ኮሚዩኒቲ አመራሮችና በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተጋበዙበት ክፍት ፕሮግራም ላይ በዝግጅቱ ከታደሙ እንግዶች ጋር ባማረ መልኩ የእራት ፕሮግራሙ ተከውኗል ።
ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሚዩኒቲ በተዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ ሁሉም አንድ ላይ በመቆምና ፕሮግራሙን በመታደም የኢትዬጵያዊነት መገለጫችን የሆነውን አንድነት የታየበት ዝግጅት አስተናግዷል። ወደፊትም ኮሚዩኒቲው ለሁሉም ተደራሽ በሚሆንበት ስራዎችን እየስራ እንደሚቀጥልም ከአመራሮቸ ተገልጿል ።
በችግር ውስጥ ለሚገኙና ድጋፍ ለሚሹ ዜጎቻችን ፣ ከዚህ በፊት በኩዌት የነበረንን መጥፎ ገጽታ ለመቀየር ፣ እርበእርሳችን ለመረዳዳት ፣ ስለሀገራችን በጎ ገጽታ ለማስተዋወቅ የግድ በኩዌት የምንኖር ኢትዬጵያኖች በአንድነትና በህብረት መስራትና አንድ መሆን ጊዜ ማይስጠው በመሆኑ የእርስ በእርስ ግንኙነቶችን ለማጠናከርም ኮሚዩኒቲው ከያዛቸው ዕቅዶች ውስጥ የመቀራረብና አንድ የመሆን ስራ ዋናው ነው። የቀድሞ የኮሚኒቲው አመራር ከሆኑት መካከል አቶ ተሰማ እንደገለፁት በቀጣይ ከኮሚኒቲው ጋር በመሆን የተቻለንን ሁሉ እንደምናግዝ ብሎም አሁን የተመሰረተው ኮሚኒቲ እየሰራ ያለው ስራ ሊበረታታ እንደሚገባ ገልፀዋል ።
ያለንን አንድነት ለማጠናከር ፣ ወደፉትም ተመሳሳይ መቀራረቦችን ለማጎልበት ታስቦ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይም ከአመታት በፊት የኢትዬጵያ ኮሚዩኒቲን ይመሩ ለነበሩ ስዎች በክብር አምባሳደር አማካኝነት ዕውቅናና ምስጋና ሰርተፍኬት ተስጥቷቸዋል ።
ከእውቅና አስጣጡ ጎን ለጎንም ክብር አምባሳደሩ ባስተላለፊት መልዕክት ሁላችንም ከኮሚዩኒቲው ጎን በመቆም ወደፊት የተሳካና ውጤታማ ስራ እንድንስራ በመረባረብ አብረን መስራት እንዳለብንና በኩዌት ለሚገኙ ዜጎችም ተደራሽ እንድንሆን በኮሚዩኒቲው እንድንዳራጅ ጥሪ አቅርበዋል ።
በእለቱ ለነበረው ድምቀት የግላቸውን ትብብር ላደረጉት የአል ሀበሻ ሬስቶራንት ባለቤት ኮሚኒቲው በዚ አጋጣሚ ላቅ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።
በዝግጅቱ ላይ ጥሪያችንን አክብራችው ለመጣችው በኩዌት ለምትኖሩ ኢትዬጵያኖች በማህበራችን ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን ።